Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Digital Library
Durbete Polytechnic College
Excellence in Technical Education
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Admin
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Digital Library
Admin Login
Facebook
Telegram
YouTube
TikTok
News Article
Latest updates and announcements from Durbete Polytechnic College
ዜና በጎ አድራጎት
December 19, 2025
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ተግባሩን እንደቀጠለበት ይገኛል።
ኮሌጁ በ2017በጀት አመት በክረምት ወራት በርካታ ሰው ተኮርና ማህበረሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ሲሰራ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን ኮሌጁ አሁንም በ2018 አዲስ አመት ይህን ተግባሩን እንደቀጠለበት ነው።
የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ሲቋቋሙና ሲመሰረቱ ለህዝብና ህዝብን ለማገልገል ነውና የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም ይህን መርህ እቅድ ውስጥ በማስገባት በርካታ ሰው ተኮርና ማህበረሰብ አቀፍ ተግባራትን ሲሰራ ቆይቷል አሁን ላይም በመስራት ላይ ይገኛል።
በዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር በፅዳትና ውበት ስራ ተደራጅተው ለሚሰሩ ከ30 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ኮሌጁ ለሁሉም ሙሉ የስራ ልብስ ቱታ በስጦታ አበርክቷል። ኮሌጁ ከዚህ በፊት ለወጣቶቹ ቋሚና አላቂ የፅዳት እቃና ግብአቶችን ድጋፍ ሲያደርግላቸው እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ከ30000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ የስራ ልብስ ቱታ ድጋፍ ተደርጓል።
የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ አቀፍ/ Community Based/ እና የበጎ አድራጎት ተግባራትን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ተቋማት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ለመስጠትና ተልዕኳቸውን በሙሉ አቅም ለመፈፀም ራሳቸውን በፋይናንስ መገንባት እንዳለባቸው ያምናል። በዚህም መሠረት ኮሌጁ የውስጥ ገቢውን ለማሳደግና የኮሌጁን ሙሉ የመሠረተ ልማት ክፍተቶችን ለመሙላት በርካታ የውስጥ ገቢ ማስገኛ ተግባራትን እየሰራ ይገኛል። በተለይም ኮሌጁ 2017/18 የምርት ዘመን በግብርናው ዘርፍ ከ 3 ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት በስንዴ ማሳ ሸፍኗል። በተጨማሪም ኮሌጁ የራሱን አሰልጣኞችና ባለሙያወችን በማስተባበር በግብርና ግቢ የዘር ብዜት ማዕከል /ነርሰሪ ሳይት/ አቋቁሞ በስራ ላይ ይገኛል።
በዘር ብዜት ማዕከሉ ከሚባዙ እፅዋቶች ውስጥ የተለያዩ የሚበሉ አትክልቶች /ማንጎ አቦካዶ ብርቱካን /፣ የደን ዛፎች፣ ጌጠኛ ዛፎች የሚጠቀሱ ናቸው።
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከግብርና ስራው ባለፈ የኮሌጁን መሰረተ ልማት ሙሉ ለማድረግ በርካታ ስራዎች በመሠራት ላይ ይገኛሉ። ከዚህም ውስጥ በኮሌጁ በሁለቱም ግቢ ዘመናዊ የመንገድ መብራት ፖውዛ ዝርጋታ ተሰርቷል፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ሁለት ዘመናዊ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ እያንዳንዳቸው 8 መፀዳጃ ክላሶችን የያዙ አንደኛው ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለተኛው ከ95% በላይ ስራው ተጠናቋል።
ተቋሙን ሳቢና ማራኪ እንዲሁም ለ2018 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ለስልጠና ምቹ ለማድረግ የውስጥ ለውስ መንገድ ስራና እድሳት ተሰርቷል።
ዱርቤቴ ፖሊ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
መስከረም 5/2017 ዓ.ም
Back to All News
Back to Home
Website developed by
Mebtu
:
0912705043