Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Facebook Telegram YouTube TikTok

ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025/EOMS ትግበራን በተመለከተ ቴክኒካል ኦዲት ድጋፍ አከናወነ።

June 16, 2026
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025/EOMS ትግበራን በተመለከተ ቴክኒካል  ኦዲት ድጋፍ አከናወነ።
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025/EOMS ትግበራን በተመለከተ ቴክኒካል ኦዲት ድጋፍ አከናወነ።

ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ድርጅቶች የአስተዳደር ሥርዓት (Educational Organizations Management System-EOMS) ስታንዳርድ ISO 21001:2025 ለመተግበር እያከናወነ ባለው ሥራ አካል ውስጥ ዛሬ ግንቦት 29/2018 ዓ.ም ቴክኒካል ኦዲት ድጋፍ ተደርጓል።


ኮሌጁ የISO 21001:2025/EOMS ስታንዳርድን ለመተግበር ቁርጠኛ ሥራ ከጀመረ ወዲህ በውስጥ ኦዲት ቡድኑ ሁለት ዙር የውስጥ ኦዲት በማካሄድ የስርዓቱን ትግበራ ሲገመግም ቆይቷል።

በዚህም መሠረት የዛሬው ቴክኒካል ድጋፍ በአቶ አለማየሁ ሰጠኝ አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን ኮሌጁ ለውጫዊ (External) ኦዲት ያለውን ዝግጁነት ለመገምገም ያለመ ነበር።

በኦዲቱ ወቅት ከስታንዳርዱ ጋር ተያይዞ በኮሌጁ የተዘጋጁ የፖሊሲ ሰነዶች፣ የEOMS ዓላማዎች (Objectives)፣ የራዕይና ተልዕኮ መግለጫዎች (Vision and Mission)፣ የኦዲት እቅዶች፣ የኦዲት ሪፖርቶች እንዲሁም ሌሎች ከሥርዓቱ ትግበራ ጋር የተያያዙ ዶክመንቶች በዝርዝር ተገምግመዋል።

በግምገማውም ወቅት የሰነዶቹ ተገቢነት፣ የስታንዳርዱን መስፈርቶች የማሟላት ደረጃ እና በተግባር የሚተገበሩበት ሁኔታ በጥልቀት ታይቷል።
በዕለቱ በተካሄደው የኦዲት መድረክ የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የዘርፍ አስተባባሪዎች፣ የEOMS ታስክ ፎርስ አባላት እና የውስጥ ኦዲት ቡድን አባላት ተገኝተው በሂደቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል።

በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን አቶ በለጠ ደምል ባስተላለፉት መልዕክት፣ በኦዲት ሙያዊ ድጋፍ የተሰጡ አስተያየቶችና ሙያዊ ጥቆማዎች በትክክል ተስተካክለው እንዲተገበሩ እና ኮሌጁ ለሚቀጥለው ውጫዊ ኦዲት በተሟላ ዝግጁነት እንዲቀርብ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት በትጋት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ኦዲት ኮሌጁ በጥራት የተደገፈ የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት እና ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ሥርዓት መስፈርቶችን በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር እያደረገ ያለውን ጥረት የሚያሳይ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
ግንቦት 29/2018 ዓ.ም
ዱርቤቴ
Website developed by Mebtu : 0912705043