Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Digital Library
Durbete Polytechnic College
Skill for today Innovation for tomorrow
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Admin
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Digital Library
Admin Login
Facebook
Telegram
YouTube
TikTok
News Article
Latest updates and announcements from Durbete Polytechnic College
በዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
June 5, 2026
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለኮሌጁ አሰልጣኞችና ዘርፍ አስተባባሪዎች በሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ዙሪያ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።
የስልጠናው ማንዋል በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በክልሉ የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ እንዲሁም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የሚያከናውኑትን የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ስራ በተቀናጀ፣ በውጤታማና በጥራት የተደገፈ መልኩ ለማጠናከርነው።
በኮሌጁ የተካሄደው ስልጠና ሁሉንም አሰልጣኞችና ዘርፍ አስተባባሪዎች በማሳተፍ የተሰጠ ሲሆን፣ በተቋሙ ውስጥ የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማሻሻል፣ የተቋማዊ ክትትልና ግምገማ ስርዓትን ለማጠናከር እንዲሁም የስራ አፈፃፀም ውጤታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል።
የኮሌጁ የጥራት ቁጥጥር አስተባባሪ (Quality Assurance) አቶ አዱኛው ስማቸው ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን፣ በስልጠናው ወቅት የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ፅንሰ ሀሳባዊ ትርጓሜዎችና መርሆዎች፣ የሱፐርቫይዘር ሙያዊ ክህሎትና ስነ-ምግባር፣ የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን የአገልግሎት አሰጣጥ ዘዴዎችና የትኩረት መስኮች፣ የፈፃሚዎች ተግባርና ሀላፊነት እንዲሁም በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በስፋት ቀርበዋል።
ተሳታፊዎችም ስልጠናው በተቋሙ ውስጥ የሚሰጡ የትምህርትና ስልጠና አገልግሎቶችን በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን እና የቁጥጥር ስርዓቱን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል።
ዱርቤቴፖሊቴክኒክኮሌጅ
የህዝብግንኙነትናኮሚኒኬሽን
ግንቦት21/2018ዓ.ም
ዱርቤቴ
Back to All News
Back to Home
Website developed by
Mebtu
:
0912705043