Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Digital Library
Durbete Polytechnic College
Skill for today Innovation for tomorrow
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Admin
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Digital Library
Admin Login
Facebook
Telegram
YouTube
TikTok
News Article
Latest updates and announcements from Durbete Polytechnic College
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በISO 21001:2025/EOMS ትግበራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሄደ::
June 5, 2026
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025/EOMS የትምህርት ድርጅቶች አስተዳደር ስርዓት ስታንዳርድን በተሟላ ሁኔታ ለመተግበርና የሁሉም ሰራተኞች ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሂዷል።
ስልጠናው በISO 21001:2025/EOMS ስታንዳርድ ክሎዝ 7.3 “Awareness” መስፈርት መሰረት የተዘጋጀ ሲሆን በኮሌጁ የሚገኙ አሰልጣኞች፣ የዘርፍ አስተባባሪዎች፣ አስተዳደር ሰራተኞች እና ሌሎች ተዛማጅ የስራ ክፍል ሰራተኞች በስፋት ተሳትፈዋል።
ስልጠናውን የኮሌጁ ISO 21001:2025/EOMS ማኔጅመንት ሪፕረዘንታቲቭ (MR) አቶ አዝመራው አማረ ያቀረቡ ሲሆን፣ በማብራሪያቸውም የISO 21001:2025 ስታንዳርድ አጠቃላይ ጽንሰ-ሀሳብ፣ የትግበራ ጠቀሜታ እና በትምህርት ተቋማት ላይ የሚያመጣው አዎንታዊ ለውጥ በሰፊው ተብራርቷል።
በተጨማሪም የኮሌጁ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ፖሊሲዎች፣ ዋና ዋና እሴቶች እና ከክሎዝ 4 እስከ 10 ያሉ የስታንዳርዱ ዋና ዋና መስፈርቶች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በተለይም የድርጅቱ አውድ፣ አመራር፣ ዕቅድ ዝግጅት፣ ድጋፍ፣ ኦፕሬሽን፣ የአፈፃፀም ግምገማ እና ቀጣይ መሻሻል ዙሪያ ጥልቅ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በስልጠናው ወቅት ተሳታፊዎች በቡድን ውይይት፣ በጥያቄና መልስ እንዲሁም በገለፃ መልክ በንቃት ተሳትፈው የስልጠናውን ውጤታማነት የሚያጠናክሩ ሀሳቦችን አቅርበዋል። ይህም የስታንዳርዱን ግንዛቤ በተግባር እንዲያዳብሩ እና በየስራ ዘርፋቸው እንዲተገብሩ አስችሏቸዋል።
በሌላ በኩል ኮሌጁ የISO 21001:2025/EOMS ስታንዳርድ መስፈርቶችን ለማሟላት በፊዚካል ኢንፍራስትራክቸር ዘርፍ የተለያዩ ማሻሻያ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል። ከእነዚህም መካከል አካታችነትን እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተጠቃሚዎች ተደራሽነት ለማረጋገጥ ራምፖችን መገንባት፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በቀለማት ውብና ሳቢ ማድረግ፣ ቀጣይነት ያለው የካይዘን ስራ ማከናወን እና ለISO ትግበራው ድጋፍ የሚሆኑ የህትመትና የባነር ስራዎችን ማከናወን ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸው ተጠቅሷል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን አቶ በለጠ ደምል በቀጣይ የሚከናወኑ የISO 21001:2025/EOMS ትግበራ ተግባራትን በየስራ ክፍሉና በየሂደቱ ፈፃሚ ባለቤቶችን በመመደብ ግልፅ የስራ ስምሪት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ሁሉም ሰራተኞች ስታንዳርዱን በአግባቡ በመተግበር የኮሌጁን የትምህርት ጥራት እና የተገልጋዮች እርካታ ለማሳደግ በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
ግንቦት 20/2018 ዓ.ም
ዱርቤቴ
Back to All News
Back to Home
Website developed by
Mebtu
:
0912705043