Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Digital Library
Durbete Polytechnic College
Skill for today Innovation for tomorrow
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Admin
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Digital Library
Admin Login
Facebook
Telegram
YouTube
TikTok
News Article
Latest updates and announcements from Durbete Polytechnic College
።ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025 የትምህርት ተቋማት ማኔጅመንት ሲስተም (EOMS) ትግበራን በይፋ ጀመረ።
April 3, 2026
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2025 የትምህርት ተቋማት ማኔጅመንት ሲስተም (EOMS) ትግበራን በይፋ ጀመረ።
(ዱርቤቴ)፦ ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሥልጠናና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችለውን የISO 21001:2025 (EOMS) ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ የትግበራ ቀን መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አውጇል።
በዕለቱ የኮሌጁ ዲን አቶ በለጠ ደምል መላው የኮሌጁ ሠራተኞች በተገኙበት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ኮሌጁ ይህንን ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ለመተግበር የወሰነው ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመንና ተወዳዳሪነቱን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል። ዲኑ አክለውም “ይህ ስታንዳርድ ተግባራዊ መሆኑ ለሰልጣኞች፣ ለሠራተኞች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት ወጥ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ቁልፍ ሚና ይጫወታል” ብለዋል።
የኮሌጁ የISO 21001:2025 ማኔጅመንት ተወካይ (Management Representative) አቶ አዝመራው አማረ በበኩላቸው፣ ስለ ስታንዳርዱ ምንነት፣ ጥቅሞች እንዲሁም በተዘጋጁ ዶክመንቶች ዙሪያ ለተሳታፊዎች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል። አቶ አዝመራው በማብራሪያቸውም ስታንዳርዱ በኮሌጁ ውስጥ እንዴት እንደሚዘረጋና የእያንዳንዱ የሥራ ክፍል ኃላፊነት ምን መሆን እንዳለበት በዝርዝር አስገንዝበዋል።
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የኮሌጁ ሠራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሰጡት አስተያየት፣ አዲሱ አሰራር የሥራ ሂደቶችን ግልጽና ውጤታማ እንደሚያደርግ በመጠቆም፣ ስታንዳርዱን በተሟላ ሁኔታ ለመተግበርና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን አስፈላጊውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳዩ አረጋግጠዋል።
ይህ የትግበራ መርሃ-ግብር መጀመር ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚጠበቅበትን ጥራት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራትና የተቀናጀ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ለጀመረው ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ተገልጿል።
Skill For Today Innovation for Tomorrow
ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
Back to All News
Back to Home
Website developed by
Mebtu
:
0912705043