Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Facebook Telegram YouTube TikTok

በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት ሲሰጥ የነበረው የሙያ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።

March 10, 2026
በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት  ሲሰጥ የነበረው የሙያ  አቅም ማጎልበቻ  ስልጠና ተጠናቀቀ።
በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት ሲሰጥ የነበረው የሙያ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።
ባ/ዳር መጋቢት 01/2018 ዓ.ም
የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ከየካቲት 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ያጠናቀቀ ሲሆን በስልጠናው ከሰሜን ጎጃም ዞን፣ ከምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከምስራቅ አዊ ዞን፣ እንዲሁም ከደቡብ ጎንደር ዞን የመጡ የፖሊ ቴ/ክ ኮሌጅና የዞን መምሪያ ሀላፊዎች እንዲሁም የስራ ቡድን አስተባባሪዎች ስልጠናውን ማግኘት ችለዋል።

እንደ አጠቃላይ የ7 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖችና የስራ ቡድን አስተባባሪዎች፣ የ18 ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖችና የስራ ቡድን አስተባባሪዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል። በዞን ደረጃ የአራት ስራና ክህሎት መምሪያ ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች ተሳትፎ አድርገዋል።

ስልጠናውን ለማጠናቀቅ ተከታታይ አመስት ቀናትን የፈጀ ሲሆን ስልጠናው ተደራሽ ያደረጋቸው ዋና ዋና ጉዳዮች 1ኛ. በጀትና ዕቅድ ዝግጅት፡ ውጤታማ የሀብት አጠቃቀምና የዕቅድ አፈጻጸም።
2ኛ. ትምህርት፣ ስልጠናና አሰልጣኝ ልማት፡ የስልጠና ጥራትን ማረጋገጥ።
3ኛ. የሰው ሀብት አስተዳደር፡ የሰራተኛውን ክህሎትና ስነ-ምግባር ማሳደግ።
4ኛ. ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የውስጥ ኦዲተር ስራን ጨምሮ ፡- የመንግስት ንብረትንና ፋይናንስ በሥርዓት መምራት።
5ኛ. የአህዝቦት (ህዝብ ግንኙነት) ስራ፡ ተቋማዊ ስራዎችን ለህዝብ ተደራሽ የማድረግ ስልቶች በስልናጠው ሂደት ላይ ትኩረት የተሰጣቸው ነጥቦች ናቸው።

በስልጠና ማጠናቀቂያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የቢሮ ሀላፊዎች እንደገለፁት የተሰጠው ስልጠና በቢሮው መዋቅር ስር ለሚገኙ ተቋሞችና ኮሌጆች የአገልግሎት አሰጣጥና ተቋማዊ አፈፃፀማቸውን የተሻለ እንደሚያደርግ የተናገሩ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም እንደዚህ አይነትና መሰል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ቀጠይነት እንዲኖራቸው አሳስበዋል።
ዱርቤቴ ፖሊ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
ባ/ዳር
Website developed by Mebtu : 0912705043