Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Digital Library
Durbete Polytechnic College
Skill for today Innovation for tomorrow
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Admin
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Digital Library
Admin Login
Facebook
Telegram
YouTube
TikTok
News Article
Latest updates and announcements from Durbete Polytechnic College
አብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ለዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ሀላፊዎች ቡድን መሪዎች እንዲሁም ለባለሙያዎች የሀቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
March 6, 2026
አብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ለዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ሀላፊዎች ቡድን መሪዎች እንዲሁም ለባለሙያዎች የሀቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው ለተከታታይ 5ቀናት ሊቆይ እንደሚችል የሚጠበቅ ሲሆን በስልጠናው በሰሜን ጎጃም ዞን፣ በደ/ጎንደር ዞን፣ በምስራቅ አዊ ዞን እንዲሁም በምዕራም ጎጃም ዞን የሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዲሁም የመምሪያ ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች በስልጠናው እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የስልጠናው ዋና አላማ በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ መዋቅር ስር ለሚገኙ የኮሌጅ ና የዞን መምሪያ አመራሮችን፣ ቡድን መሪዎችንና በተዋረድ ያሉ ባለሙያዎችን የመፈፀም አቅማቸውን ለማሳደግና አዳዲስ አሰራሮችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደሆነ ተገልጿል።
ስልጠናው በዋናነት በበጀትና ዕቅድ÷ በትምህርትና ስልጠና እና የአሰልጣኝ ልማት ዙሪያ÷ የሰው ሀብት አስተዳደር÷ የንብረት አያያዝና አጠቃቀም÷ የአህዝቦት ስራን በልዩ ትኩረት ስለመፈፀም በሚመለከት የሚያተኩር ስልጠና እንደሚሰጥ በመድረክ መክፈቻ ፕሮግራም ላይ ተገልጿል።
ዱርቤቴ ፖሊ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
ባ/ዳር
Back to All News
Back to Home
Website developed by
Mebtu
:
0912705043