Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Digital Library
Durbete Polytechnic College
Skill for today Innovation for tomorrow
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Admin
Home
News
Programs
OBT
Admission
Trainers
About
Events
Contact
Digital Library
Admin Login
Facebook
Telegram
YouTube
TikTok
News Article
Latest updates and announcements from Durbete Polytechnic College
የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አከናወነ።
February 18, 2026
የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት አመት የ 6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ ያከናወነ ሲሆን በኮሌጁ በበጀት አመቱ በእቅድ ተይዘው የተፈፀሙ ተግባራት መላው የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል።
ኮሌጁ በበጀት አመቱ ከመቸውም ጊዜ የተሻለ በርካታ ተግባራትን የፈፀመ ሲሆን በተለይም ከወረዳና ከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን ቀጣይ የከተማ ልማት ስራዎችን ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቋል።
የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ISO 21001:2025 EOMS/ Educational organization Management System/ ብቁ ለመሆንና ስታንዳርዱን ለማስተግበር የሰራተኛውን ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ የጀመራቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት በጥሩ ሁኔታ እየተናወኑ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።
በበጀት አመቱ ኮሌጁ በጥንካሬ ከገመገማቸው ተግባራት መካከል የተከናወኑ በርካታ ሰው ተኮርና ማህበረሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ተግባራት የሚደነቁ ናቸው ።
የኮሌጁን አቅም በፋይናንስ መገንባት ጋር በተያያዘ በ2018 በጀት አመት በርካታ የውስጥ ገቢ ማስገኛ ተግባራት ተሰርተዋል በዚህም መሰረት ኮሌጁ በግብርናው ዘርፍ በፈፀማቸው የልማት ስራዎች በበጀት አመቱ እስከ ግማሽ አመት ባለው ጊዜ ውስጥ በግብርና ስራ ብቻ ከ450,000 ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ በሪፖርቱ ቀርቧል።
በእለቱ የስራ አፈፃፀም ግምገማው ከተከናወነ በኋላ ለመላው የኮሌጁ ሰራተኞች የተለያዩ የሀቅም ግንባታ ስልጠናዎች ማለትም ድጅታል አማራ ኢንሸቲቭ እንዲሁም የኢትዮጽያ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጅ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።
በቀረበው እቅድና አፈፃፀም ግምገማ እንዲሁም በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጅ ዙሪያ ከቤቱ በተነሳው ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች ላይ የኮሌጁ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።
ዱርቤቴ ፖሊ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
ጥር 28/2018ዓ.ም
Back to All News
Back to Home
Website developed by
Mebtu
:
0912705043