Phone: +251 582230475
Email: drptc2001@gmail.com
Facebook Telegram YouTube TikTok

Global Enterpreunership Week/አለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንት በዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

December 21, 2025
Global Enterpreunership Week/አለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንት በዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Global Enterpreneurship Week/GEW/ አለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንት በስራ ፈጠራ ስልጠና ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። በዚህም መሰረት የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሁለተኛ ዙር የስራ ፈጠራ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ Global Enterpreneurship Week/አለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንትን/ ምክንያት በማድረግ የስራ ፈጠራ ስልጠና በመስጠት ላይ ሲሆን ኮሌጁ በመጀመሪያው ዙር በደቡብ አቸፈር ወረዳና ዙሪያ ቀበሌ ለሚገኙ 496 ለሚሆኑ ወጣቶች ለሁለት ተከታታይ ቀናት የስራ ፈጠራ ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል። በሁለተኛው ዙር ስልጠና ደግሞ በዱርቤቴ ከተማ ለሚገኙ ለ257 ወጣቶች ስልጠናውን እየሰጠ ይገኛል።ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የሚቆይ ሲሆን የዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የዱርቤቴ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከEnterpreneurship Development Institute/ EDI/  ጋር በመተባበር የአለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንትን (GEW) መሰረት ያደረገ የስራ ፈጠራ እና  የንግድ ክህሎት ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
ስልጠናው ስራ የሌላቸው እና ስራ  ጀማሪ ወጣቶችን ክህሎት በማሳደግና የስራ ፈጠራ አቅም ክፍተቶቻቸውን በመሙላት ወደ ስራው አለም እንዲቀላቀሉ የሚያስችል የስራ ፈጠራ ፣ የንግድ ስራ ማጎልበቻ ስልጠና ነው።

የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) የዓለም አቀፍ የስራ ፈጠራ ሳምንትን በማክበር ከክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ተዋረድ ካሉ ጽ/ቤቶች እና ከዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በሁለት ዙር እየተሰጠ ባለው ስልጠና  በዱርቤቴ ከተማ እንዲሁም በደቡብ አቸፈር ወረዳ ዙሪያ ቀበሌዎችን ጨምሮ ለ753 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎችና አዲስ ስራ ፈላጊ ወጣቶች በዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አማካኝነት በስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል።

የዱርቤቴ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ት/ት እና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ በቀለ ሀይሉ በስልጠና ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ይህ ስልጠና ለነባር ኢንተርፕራይዞች ብቻ ሳይሆን ወደፊት ወደ ሥራ እንዲገቡ ለምናግዛቸው ስራ ፈላጊ ወጣቶች ጭምር አየተሰጠ ሲሆን ወጣቶች አደረጃጀት አየተፈጠረላቸው እና አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው ወደ ስራ እንደሚገቡ ይፈለጋል። ስለሆነም ነባር ኢንተርፕራይዞችም በገበያ ውስጥ የተሻለ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ድጋፍ ጽ/ቤቱ የሚችለውን ድጋፍና ክትትል የሚያደረግላቸው መሆኑን ገልፀው በተጨማሪም ሰልጣኞች ስልጠናውን ከጨረሱ በኋላ የስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የብድርና ቴክኒካል ድጋፍ አገልግሎት
እንደሚመቻችላቸው ተናግረዋል።

ዱርቤቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
ህዳር 12/2018 ዓ/ም
Website developed by Mebtu : 0912705043